addis ababa

በመዲናዋ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ ተደረገበት

የካቲት 19, 2012 ዓ. ም       

ማህበራችን የከባድ መኪና ተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የሰአት ገደብን አስመልክቶ ጥናት ካስጠና በኋላ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ፤ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፤ ለትራንስፖርት ሚኒስቴር ፤ ለገቢዎች ሚኒስቴር እንዲሁም ለክቡር የአዲስ አበባ ከንቲባ ያቀረበ ሲሆን ይህንኑ ጥናት ከነመፍትሄ ሀሳቦቹ ተግባራዊ ለማስደረግ ተካታታይ ውይይቶችን ከ3 ወራት በላይ ለሆነ ጊዜያት ክትትል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ከ20/06/2012 ዓ.ም ጀምሮ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓትማሻሻያ አድርጎበታል፡፡
በአዲሱ ማሻሻያም ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።

ይህን ውሳኔ ለማግኘት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከማህበሩ ፅ/ቤት ጋር ሆነው ሲሰሩ የቆዩትን የቦርዱን አመራር እያመሰገንን በቀጣይም ስራዎች አባላት ድጋፋችሁ እንዳይለየን በማክበር እጠይቃለሁ፡፡ ማህበራችን ያስጠናው ጥናት ለሌሎችም ሴክተሮች ውጤት እንዲገኝ ረድቷል ፡፡
                                                                                                                             

ከሠላምታ ጋር
አሸናፊ መርዕድ
 


Print   Email